ምርጥ እና ዘመናዊ የጥርስ ህክምና ማዕከል
የስዊዝ እና የጀርመን ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመን፣ ልዩ እንክብካቤ እና አስተማማኝ ህክምና የምንሰጥበት ማዕከል።
እንኳን ወደ ግሪን ላይፍ ስፔሻሊቲ የጥርስ ክሊኒክ በደህና መጡ። ክሊኒካችን ዘመናዊ የጥርስ ህክምናን ከልዩ አቀባበል እና እንክብካቤ ጋር አጣምሮ የያዘ ነው። ልምድ ባላቸው ባለሙያዎቻችን አማካኝነት ደህንነትዎን እና ምቾትዎን በጠበቀ መልኩ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና ለመስጠት ዝግጁ ነን።

ዶ/ር ሮቤራ ጫላ
DMD፣ ረዳት ፕሮፌሰር እና የክሊኒኩ ስራ አስኪያጅ
“ተፈጥሯዊ ጥርስን ማዳን ሁልጊዜ ከመንቀል ይቀድማል! የቱንም ያህል ውድ የሆነ የጥርስ ተከላ ቢደረግ የተፈጥሮ ጥርስን ሊተካ አይችልም። ዋነኛ አላማችን ጥርስዎን ማዳን ነው።”
ጥርስን ከመንቀል ማዳን ይቀድማል
በግሪን ላይፍ የጥርስ ክሊኒክ ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት ቀድሞ መከላከል ላይ ትልቅ ትኩረት እንሰጣለን። ለዚህም የጥርስ መበስበስ ምርመራዎችን፣ መደበኛ የጤና ክትትሎችን እና የጥርስ እጥበት አገልግሎቶችን እንሰጣለን። ከዚህም በተጨማሪ ልምድ ባላቸው ሀኪሞቻችን የነርቭ ህክምና፣ የጥርስ ማስተካከል (ብሬስ እና አላይነር)፣ የጥርስ ተከላ እና የውበት ህክምናዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘን እንሰጣለን።
የጥርስ መበስበስ ምርመራ
ጥርሶ ላይ ህመም ከመጀመሩ በፊት የጥርስ መበስበስን በዘመናዊ ካሜራ ቀድሞ መለየት።
የጥርስ እጥበት እና ጽዳት
ጥርሶን ሳይጎዱ ዘመናዊ በሆነ መንገድ የጥርስ ዝገትን እና ቆሻሻን ማጽዳት።
የነርቭ ህክምና በካሜራ ታግዞ
በጣም የተጎዱ ጥርሶችን በካሜራ (ማይክሮስኮፕ) በማየት ከመነቀል ማዳን።
የጥርስ ተከላ እና ልባስ
ከእውነተኛው ጥርስዎ ጋር የሚመሳሰሉ ጠንካራ እና ውብ የሆኑ የጥርስ ተከላዎች እና ልባሶች።
ምርጥ እና አስተማማኝ ህክምና
ህክምናዎን ያለስጋት እና በምቾት እንዲከታተሉ የሚያደርጉዎት 4ቱ የክሊኒካችን መለያዎች።
ለእርስዎ የተለየ እንክብካቤ
ቅድሚያ ለምቾትዎ እና ለደህንነትዎ እንሰጣለን
እያንዳንዱን ታካሚ በፍቅር እናስተናግዳለን። ህመም የሌለው የማደንዘዣ ዘዴ በመጠቀም ፍርሃትዎን እናስወግዳለን፤ እንዲሁም ከበጀትዎ ጋር የሚስማማ ግልፅ የሆነ የህክምና እቅድ እናወጣለን።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ
የስዊዝ እና የጀርመን የጥርስ ህክምና እቃዎች
የድሮውን የጥርስ መለኪያ ፕላስቲክ ያስቀረውን ዘመናዊ የ3D ካሜራ (ስካነር)፣ ጉዳት የሌለው ዲጂታል ኤክስ-ሬይ እና የጀርመን ማይክሮስኮፕን እንጠቀማለን።
ልምድ ያላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞች
በየዘርፉ የተካኑ የጥርስ ሀኪሞች አሉን
በዶክተር ሮቤራ ጫላ የሚመራው የሀኪሞቻችን ቡድን የጥርስ ማስተካከል፣ የቀዶ ጥገና፣ የነርቭ ህክምና እና የህጻናት ጥርስ ስፔሻሊስቶችን አቅፎ የያዘ ነው።
የተሟላ የጥርስ ህክምና አገልግሎት
ሁሉንም የጥርስ ህክምና በአንድ ቦታ
የህፃናት ጥርስ ህክምና፣ የጥርስ ተከላ፣ የጥርስ ማስተካከል (ብሬስ እና አላይነር)፣ እንዲሁም የጥርስ ውበት ህክምናዎችን በአንድ ቦታ እናቀርባለን።
ታካሚዎቻችን ክሊኒካችንን ለምን ይመርጣሉ?
ዘመናዊ ህክምናን ከተመጣጣኝ ዋጋ እና ከጥሩ አቀባበል ጋር በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ እናቀርባለን።
አስተማማኝ የጥርስ ህክምና
ልምድ ያላቸው ሀኪሞቻችን ጥራታቸውን የጠበቁ እቃዎችን በመጠቀም አስተማማኝ ህክምና ይሰጡዎታል።
ምቹ እና ዘና የሚያደርግ ቦታ
ለታካሚዎቻችን ምቹ፣ ንፁህ እና ዘና የሚያደርግ ቦታ ስላዘጋጀን ፍርሃት ሳይሰማዎት ይታከማሉ።
ተመጣጣኝ ዋጋ እና ዱቤ አለ ክፍያ
ሁሉም ሰው ጥራት ያለው የጥርስ ህክምና ማግኘት አለበት ብለን ስለምናምን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እናያለን። በተጨማሪም በ0% ወለድ 'በዱቤ አለ' የመክፈል አማራጭ አዘጋጅተናል።
ለውጡን በእራስዎ ይመልከቱ
የሰራናቸውን ስራዎች ለማየት ምስሉን ወደ ግራ እና ቀኝ ያንሸራትቱ።


ለህክምና የተሟሉ እቃዎች
የጥርስ ህክምና አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ?
ከሀኪሞቻችን ጋር አሁኑኑ ቀጠሮ ያስይዙ።